Jump to content

User:Akibeth

From Wikipedia, the free encyclopedia

በቤቱ ላላችሁ

የተላከ ደብዳቤ

(ግጥም በአክሊሉ ፍስሐ)

" ያለ ሥርዓት የሚሄዱትን ገሥጹአቸው፤ ድፍረት የሌላቸውን አጽኑአቸው፤ ለደካሞች ትጉላቸው፤ ሰውን ሁሉ ታገሡ።"

(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 5:14)

እኔ ደካማ ነኝ መቆም የተሳነው ምግባሬ የከፋ

ጽድቁን የዘነጋው መንገዴን የሳትኩኝ ብርሃኔ የጠፋ

በዓለም ጉራንጉር እየተወሸኩኝ በሐሳዊ ፍቅሯ አስራኝ አንቀላፋሁ

በማይመስለኝ ትርክት የእኔ ባልሆነ ውስጥ ተዘፍቄ ለፋሁ

በዓለም ጨለማ ሰውነቴ ሰጥሞ ህሊናዬ ቢያድፍ

በእርባና ቢስ ኑሮ በማይነጋ ለሊት ሕይወቴን ብገድፍ

በሞትና መኖር እየተንገዳገድኩ መካከል ላይ ቁሜ

በኃጢት አረንቋ የተጨማለቀች ሕይወት ተሸክሜ

ስኳትን ስለፋ ለማትሞላዋ ዓለም ከሞት ጋር ስታደም

ፍቅሩን እረስቼ የጥላቻን ወሬ ክፋት ሳገለድም

እውቁኝ እንግዲህ

እኔ ማለትኮ መንገድ የጠፋበት ዓይን ያለው ዓይን አልባ

መሪ ሚያስፈልገኝ ወደ ተቀደሰው ቅጽርህ እንድገባ

ሕዝነ ህሊናዬ ማስታዋል ተስኗት ቃልህን ተርባ

እኔ ማለት እኮ

ነግቶ እየመሸ ተሸክሜ ምኖር  ኃጢያት ያደለበው የስጋ ገላባ

አምላክ ሆይ ምሕረትህ ይቅርባይነትህ ካልሠራኝ መልሶ

እኔኮ የለሁም ከጠፋሁ ቆይቷል አካላሌ ተድሶ።

አዎ ዛሬ እግር ጥሎኝ ከደጁ ብመጣ

በንፋስ ሚወሰድ ያሸዋ ላይ ሥሪት ነውና አካሌ ለመፍረድ አትሩጡ

ገና ከመቆሜ ደግሞ መጣ በሚል በእኔ መመለስ ሰዎች አትቆጡ

ኃጢአተኛነቴን ጥፋተኛነቴን አምናለሁ አልክድም አትጠቋቆሙ

የትላንቱ ግብሬ በንስሃ ታጥቧል ጸለዩልኝ እንጂ ዛሬዬን አትሙ

*

እባክህ ወንድሜ  ''አንተ ገልቱ ፍጡር ምንም የማትረባ'' ብለህ አትምከረኝ

እኔም አውቀዋለሁ ምግባሬ ጥፉ ነው እርሱን አትንገረኝ

ከተቻለህማ በቅኑ ጎዳና በመመለስ መንገድ ወደ ቤቱ ምራኝ

ትጉሁ ወንድሜ ስለድንግል ማርያም ስለ አዛኚቷ ዳግም እንደገና በጸሎት አሠራኝ

ጌታ እንደሰበከው ፍሪዳ ቢታረድ ስለጠፋ ልጁ ለመመለስ ዜና ቢጣልልኝ በጉ

የሰማይ መላዕክት እሰይ እሰይ ብለው በእኔ መመለስ ደስታን ቢሰርጉ

ቢያለብሰኝ አባቴ በወርቅ የከበረ ጥሩርና ካባ

አይክፋህ ወንድሜ ይቅርታን ተችሬ ከደጁ ስገባ

አንተ ማለት እኮ

''ስትሴስን የኖርክ ሁሉንም የፈጸምክ ኃጢያት ያደከመህ

ገንዘብ ያጠመደህ የማትረባ እኮነህ''

አትናገሪብኝ እንዲህ ብለሽ እቱ ለቀረበሽ ሁሉ  የጥፋቴን ዝርዝር

ጽድቅሽ እንዳያድፍ በእኔ መጻተኛው በሰጠመው ክብር

አዎ እህቴ ሆይ አይነጻጸሩም ነፍስሽ እና ነፍሴ

አንቺ ማለት እኮ ፍጹም የማትጠፊ ደጁ ለቅዳሴ

ይህንን አውቄ ከቤቱ የቆምኩት ምሕረትን ፍለጋ

ሰልችቶኝ ስቃዬ በጸለመ እልፍኝ አምሽቼ ሳነጋ

የመጣሁትማ ከእንግዲህ በኋላ ከአምላክ ታርቄ ለመኖር ዘላለም

ከዚህ የበለጠ የነፍሴን ጩኸቷን የሚመልስ የለም

አሳስሮ ያስቀረኝ የዓለም ገንዘቧ ጌጧ ቲርኪምርኪው

ኃጣያተኛ ነፍሴን ባንቺ ቅድስና ንጹኋ እህቴ ሰፍረሽ አትለኪው

መሽቶብኛልና እንዲሁ ስኳትን ለስጋ ምቾቴ  በዓለም ገበያ

ሳልቆም ጨላለመ በንጹህ ልቦና ከጽድቁ ማደያ

የእኔ ሚዛንማ ኃጢያት ያመዘነው እንደሆነ አውቄ

ልመናን ማቅረቤ በጸጸት ማንባቴ ከደጁ ወድቄ

ሌላማ ምን አለኝ እንዲሆነኝ እንጂ ምሕረቱ ድህነት

ዓለም አወኳት እንደሆነች ምክነት

ተይ እህቴ ህይ

ካንቺ ቅዱስ ስጋ ነጋ መሸ ደጁ ቁሞ ከጸለየው

የሚያወዳድረኝ የሚያፎካክረኝ  የትኛው ግብሬ ነው።

አዎ

እናላችሁ ሰዎች መምጣቴ አይታችሁ ልቤ ተመልሶ

በቅዱሳን ጸሎት በማርያም ምልጃ ሕይወቴ ታድሶ

እስከ ከርሞ ድረስ በሚል ውብ ድምጻቸው ሕይወቴ ተምራ

ክፋቴን ሳይቆጥር በቀናት ላይ ለእኔ ዛሬ ተጨምራ

ወደ ቅጥሩ ስቀርብ ዓለም ያደከመኝ የጠፋውት ልጁ

በአንድ አትታድሙ አትበሉኝ ባካችሁ  'ይውጣልን ከደጁ'

በእኔ በኃጢያተኛው የከሰመች ሕይወት በዓለሙ ምርኮኛ

ጽድቃችሁ አይርከስ ለሃሜት አትትጉ አትሁኑ ምደኛ

አዎ

ብመጣ በጸጸት በእንባ ታጅቤ በመመለስ መንገድ

በቀደመ ግብሬ አንተ ልጅ በማለት ወጃጄ አትፍረድ

ጸልይልኝ እንጂ የቀረበው ልቤ ዳግም እንዳይጠፋ

በእኔ መመለስ ታላቁ ወንድሜ ባክህ አትከፋ

እናልሽ እሕቴ ገብቶኛል ጥፋቴ ይኸው ዛሬ ደርሶ

መኖርን እሻለሁ በእግዚአብሔር እቅፍ እንባዬ ታብሶ

ባዛኝቷ እመቤት በድንግል እናቴ ክብሬ ተመልሶ